Twinkle twinkle, little star, how I wonder what you are…. No, really – what are stars made of and how did they get all the way up there in the sky? Let’s find out more with astrophysicist, Dr Kirsten Banks! Get ready to blast off in 5, 4, 3, 2 1!
Player FM - Internet Radio Done Right
Checked 1y ago
تمت الإضافة منذ قبل three أعوام
المحتوى المقدم من Leoul Zewelde. يتم تحميل جميع محتويات البودكاست بما في ذلك الحلقات والرسومات وأوصاف البودكاست وتقديمها مباشرة بواسطة Leoul Zewelde أو شريك منصة البودكاست الخاص بهم. إذا كنت تعتقد أن شخصًا ما يستخدم عملك المحمي بحقوق الطبع والنشر دون إذنك، فيمكنك اتباع العملية الموضحة هنا https://ar.player.fm/legal.
Player FM - تطبيق بودكاست
انتقل إلى وضع عدم الاتصال باستخدام تطبيق Player FM !
انتقل إلى وضع عدم الاتصال باستخدام تطبيق Player FM !
المدونة الصوتية تستحق الاستماع
برعاية
Sost kilo explicit
وسم كل الحلقات كغير/(كـ)مشغلة
Manage series 3372843
المحتوى المقدم من Leoul Zewelde. يتم تحميل جميع محتويات البودكاست بما في ذلك الحلقات والرسومات وأوصاف البودكاست وتقديمها مباشرة بواسطة Leoul Zewelde أو شريك منصة البودكاست الخاص بهم. إذا كنت تعتقد أن شخصًا ما يستخدم عملك المحمي بحقوق الطبع والنشر دون إذنك، فيمكنك اتباع العملية الموضحة هنا https://ar.player.fm/legal.
وسم كل الحلقات كغير/(كـ)مشغلة
Manage series 3372843
المحتوى المقدم من Leoul Zewelde. يتم تحميل جميع محتويات البودكاست بما في ذلك الحلقات والرسومات وأوصاف البودكاست وتقديمها مباشرة بواسطة Leoul Zewelde أو شريك منصة البودكاست الخاص بهم. إذا كنت تعتقد أن شخصًا ما يستخدم عملك المحمي بحقوق الطبع والنشر دون إذنك، فيمكنك اتباع العملية الموضحة هنا https://ar.player.fm/legal.
كل الحلقات
×#Spotify #Sostkilo #shortstory
ሮማናት – ናሽናል ካፌ . . . ሮዝ አገሯ ያለ ካፌ ስትቀጥረኝም ሆነ ቀጥራኝ ስትቆይ ለመጀመሪያ ግዜ ነው ። እንደደረስኩ ወፍራም የማሽን ቡና አዝዤ እሱን እየጠጣሁ ጥበቃዬን ጀመርኩ ። ካፌው ውስጥ ዝንቦች እንዳያስቸግሩ በሚል በየጠረጴዛው የሊም ቅጠል ተነጥፏል ። ውስጥ የሚተራመሰውን ሰው ...
የ መ ን ታ ፡ እ ና ት ፡ ፖ ለ ቲ ካ [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ] ለማበጠር ጀምራው ከነበር ፀጉሯ ውስጥ እጇን ወትፋ "ዋ………ይ"ብላ ጮኸች ። እሪታዋ ርዝመቱ በመሃል ቅላፄዋ እስኪለዋወጥ ነበር ። ጩኸቷን ተከትሎ ቤቱ ውስጥ ፀውታ (*ፀጥታ + ክውታ) ሰፈነ ። የድንገት ጩኸቷ ከሷ በፊት ሲርገበገቡ የነበሩ ሁለት የመንትዬ እንጥሎችን አርግቧል ። ሣራ ያለግዜ የመጣችባት ፅጌዋ(*ፔሬዷ) ምቾት ነስታት ድምፅ የሚባል ነገር መስማት አስጠልቷታል። አንዴ አግና በለቀቀችው ጩኸቷ ያሰፈነችውን ፀውታ ቶሎ ለመጠቀም አሰበች ። ከጆንያ ላይ ሃባ ክር መዛ ልጆቿ የተጣሉበትን ፊኛ የኮመዲኖው ጠርዝ ላይ ቋጠረችው። ድምር ለቅሷቸው ሲያስጨንቃት ወላ ፊኛውን መደንቆል ዳድቷት ነበር ።… ጧ! አርጋ አፈንድታ - ሠላሟን ያገኘች እንደው - ግን መጮህን መረጠች ። ፊኛው ላይ እንደማይደርሱ ያወቁት አልቃሻ ልጆቿ በድንገቴ ቃጠሎ ጩኸቷ ተደናግጠው ለአፍታም ቢሆን እንደማደብ አሉ ። ለቅሷቸውን እንደፍሬን ቀጥ ማድረግ አሳፍሯቸው ነው መሰል ተንፈሳፍሰው ባላዝኖት ዋጡት ። ረጭታውና የቤቱ ሰላም የቆየው ግን ለግማሽ ደቂቃ ነበር ። በሰማያዊው ኮመዲኖ ተደብቃባ የነበረችው እጀ'ዱሽ አሻንጉሊት (ታቲ ነው የሚሏት) ላይ አይናቸው እስክታርፍ ። አሻንጉሊቷ የተደበቀችበት ምክንያት መሳይ ጓደኛዋ (ቲታ) ጠፍታ እሷንለሁለቱም ማካፈል ከባድ ስለነበር ነው ። ልክ ታቲን እንዳዩ የለቅሷቸው መቀጣጠያ ሌላ ጋዝ ሆነች ። ( *ሰው አይገባውም እንጂ መንታ ማሳደግ አንድአይነት ልብስ ከማልበስ የዘለለ ፖለቲካ ነው ። ዲፕሎማሲ ሳይችሉ እንዴትም የመንታ እናት አይኮንም) * * * ዛሬ ፥ የመንትየዎቹ ኢዛና'ና ሣይዛና አራተኛ ዓመት የልደት በዓል ነው ። አራቱ ዓመታት ምኔ እንደንፋስ እንዳለፉ ጭራሽ አታውቅም ። የእያንዳንዷ ቀን ርዝመት ግን ማለቂያ አልነበረውም ። ሌት ተኝታ ካደረችበት እንቅልፍ ባይኗ ሳይዞር ያነጋችው ይበልጣል ። እንዲህ ያማረ ድግስ በቤቷ ስታዘጋጅ የመጀመሪያዋ ነው ። ሳምንት ሙሉ ስታስብበት ከርማ እንደሚሆን ለማድረግ አንድ ለናቷ የቀረቻትን አምሳ ብር ፈነከተች። ቅዳሜ ደርሶ ደሞዝ እስክትወስድ መቆያ ቤስቲን እንደሌላት እያወቀች ለልደታቸው የሚሆኑ ነገሮችን ገዛዝታ እጇ ላይ የቀራት አስራ ስድስት ብር ነው ። ሆኖም ከድግሱ ኋላ ስለሚመጡ ግጥ ቀናት ማሰብ ጭራሽ አትፈልግም ። ቲታ (አሻንጉሊቷ) የቆሰቆሰችውን ለቅሶ ገላቸውን በማጠብ ሸውዳ ከሐይቅ የታጨደ ለምለም ገሣ ትጎዘጉዝ ገባች ። መብል ከመደርደሯ ቀድማም የልብስ ሳጥኑን በመጎተት እንደጠረጴዛ የቤቱ መሃል ላይ አኖረችው ። በዘይት የተሟሸ ድስት ውስጥ የዘራችውን ፈንዲሻ በክዳኑ እንዳፈነች አፈካች ። እምትሰራበት ዳቦ ቤት ያስጋገረችውን ኲንስንስ ህብስትም አማትባ ቆራረሰች። ( * ቄስ ቢጠፋ ወንድ … ወንድ ጠፋ ተብሎ ዳቦ ሣይቆረስ አይቀር ) ይህ ሁሉ ሲሆን የተጠራ ሰው አልነበረም ። ድግሡ የቤተሰብ ነው ፤ የእማይቷና የደቋ ብቻ ። አራት አመት ዝዋይን መባጃ (*ላልቶ ሲነበብ መቆያ እንደማለት) አርጋት ስትኖር ከልጆቿ በቀር ከሰው አክርራ የገጠመችበት ግዜ አታስታውስም ። ጠፍታ እንደመምጣቷና ላገሩ አዲስ እንደመሆኗ አንገቷን አቀርቅራ ወጥታ አፏን እንደለጎመች ትመለሳለች ። ንጭንጯ - መከፋቷ -ማልቀሷ - ሚስጥሯ ፤ ሁሉም በሯን ከዘጋች በኋላ ነው ። ይሄ ፥ ጥሩ የሽቦ አጥር ሰራላት ። እንደ ስውር ክፈፍ እንግዶችን አርባ ክንድ ከሷ አራቀ ። አሁን…ያለፈ ታሪኳን የሚገምት እንጂ የሚያውቅ ባገሩ አንድ አይገኝም። ሣራ የፅንስ አፍይ እርሾዋን ዝዋይ አልተቀበለችም ። ወደዝዋይ ከመውለዷ ስምንት ወር ቀድማ ነው የመጣችው። የመጣች ሰሞን የነበራትን ወዝ እንዲ በአራት ዓመት ረግፎ ያልቃል ብሎ የገመተ የለም ። ገላዋ - ደም ግባቷ - የፈገግታዋ ስርጉድ - ከስከሶ ፀጉሯና ድምቡሽ ቂጧ ፤ ለከተማው ገልዋዳ ሁሉ አፍ ማስከፈቻ ነበር ። ማርገዟ እየለየ ሲመጣ - ከንፋስ እንደሻለች (*ሽል እንደያዘች) ሁሉ የአባትየውን ማንነት በሆዷ አብታ ኢዛናንና ሣይዛናን ተገላገለች። ጎረባብቶቿም በጀርባዋ ይንሾካሾኩ እንጂ ደፍረው አልጠየቋትም ። ነገሩ 'ምስኪን የማርያም አራስ' ብለው ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ ሙያም የላቸው ። * * * ለሆነ ንግስ (*ለገብርዔል መሰለኝ) ለኩሳው ግማሹ የቀለጠ ሻማን ከመስኮት ጠርዝ አውርዳ ሳጥኑ ላይ አስቀመጠች ። ይህን ያዩት ልጆቿ ለልደታችን አዲስ ሻማ ካልተገዛ የሚል ሌላ ንጭንጭ ጀመራቸው ። ንጭንጩ ወደለቅሶ ከመቀየሩ ቀድማ ወጣችና ሁለት ሻማ ገዝታ ገባች ። ስትመለስ እጇ ላይ አስራ አንድ ብር ቀራት ። መዳህና መደገፍ ከጀመሩ ወዲህ ቀኑን ሙሉ ስትጯጯህ ነው የምትውለው ። የልጆቿ ኃይል ግን ከእርሷ በአእላፍ ይበልጣል -የመቶ ባትሪ ድንጋይ ጉልበት ነው ። ሣይዛና አልጋ ላይ ለመውጣት የተነጠፈ አልጋ ከሳበ ኢዛና በጆግ ያለ ውሃ ይደፋል ። አንደኛው የጫማ ሶል አፉ ውስጥ ሲከት አንደኛው የተጣለ ማስቲካ ፀጉሯ ላይ ይለጥፍባታል ። አንዱ ሥኳር በትኖ ከላሰ ሌላኛው ጋወኗ ላይ ኩባያ ደፍቷል ። (*እናት ስድስት እጅ ነው ያላት - ይሉት ተረት ቀልድ አይደለም) አንዳንዴ ይደክማታል ። ድካም አይሉት ከባድ ድካም ። አለ አይደል አዙራ የለበሰችውን ቲሸርት አስተካክላ ለማድረግ ሀይል እስከማጣት ድረስ ። ይኼኔ ያለአባባይ ለሰዓት ታለቅሳለች ።በድሎት ተጨንቃ ያደገች ልጅ ሻሽ የክቷ ሆኖ ስታገኘው -በማታቀው ከተማ ያለአንድ ዘመድ ስትኖር - እናትም አባትም ስትሆን - እጣፈንታዋ ከጠርዝ ሲወጣ …እንዴት አታለቅስ ? ይዛ የገባችውን ሻማ ለኮሰች ። የለኮሰችበትን ክብሪት ወዝውዛ አጠፋችና እንደማይክ ከአፏ በመደቀን " ክቡራትና ክቡራን የሣራ ተስፋይ ቤተሰቦች - እናታችሁ ለልደታችሁ ሲባል ከኡዝቤኩስታን ካስመጣችው ባንድ ጋር አብራ ታቀነቅናለች " አለች ። ሣይዛና ከአፏ ተቀብሎ "ኡዝቤኩቲሲሲዛን እንደኛ መንታ አለ ? …እማዬ " ። ለመልስ ማሰቢያ ግዜ ሳይሰጣት ሌላኛውን ጥያቄ በዛው ቀጠለ ። "እኛ ግን ለምንድን'ነው መንታ የሆነው ?" በድካም ውስጥ ሆናም ቅብጠታቸው እንጂ ጥያቄያቸው ሰልችቷት አያውቅም ። " እግዛብሄር ሁላችንንም ሲፈጥር በርሱ አምሳል ነው የሠራን - እና አንዳንዴ የሆነ ፊት ይሰራና በጣም ከወደደው… ይደግመዋል ። ከዛ … መንታ ይፈጠራል ማለት ነው ። " ወሬዋን ጨርሳም እንድትቀጥልላቸው ፊታቸውን እያብለቀለቁ ያይዋታል ። ስትወዳቸው ለጉድ ነው …አታበላልጥም ። ሳይዛና እንቅልፋም ስለሆነ ምናልባት እሱን የበለጠ ሳትወድ አትቀርም። (*ይህን ለመረዳት የመንታ እናት መሆን ያስፈልጋል) አይን አይናቸውን እያየች "… ሃፒ በርዝ ደ…'' ከማለቷ ከማዳበርያ በተሰራው ኮርኒስ ውስጥ የሚንሸራሸሩት አይጦች መዝሙሯን ለሁለተኛ ግዜ አቋረጧት ። እንዳልበረገገች ሁሉ ራሷን አጀግና " ለ…ሙሽሪት … ማንን ልዳርላት ? " አለቻቸው ። አውቀውባታል ፤ የሷን ያህል አይጥ የሚፈራ በቤቱ የለም ። እንደጀርባዋ ታሪክ*(የማይነገር/የማይፃፍ) በዋነነት የምትፈራው ወንድን ልጅ ነው ። ፂም አብቃይ ሁሉ ቀንድ የቀረው አውሬዋ ነው ። የፈጣሪዋ ግፍ ይባስ ጭራሽ ሁለት ተብዓት ከማህፀኗ አሸከማት ። በሆዷ ዓመት ቀረሽ ወራት የፀነሰቻቸውን ....…
Leoul Zewelde የሮም ወታደሮች እየተዟዟሩ ሶስቱ ዛይሎኖች ላይ ቅናዋት ሲወቅሩ ይታየናል በሩቅ … ከካህናት ዕሠይ ፤ ካይሁድ ጉርምርምታ አልፎ የሚረብሽ የአንዲት ሴት ስቅስቅታ ይሠማናል ከሩቅ … ለተጓዥ አላውያን መንፈቅ ትርዒት ፥ ከሩቅ ለምናየው …የአርብ መንገድ አድክሞን ከመስቀሉ ጀርባ ተጋርደን ለቆምነው … ክርስትና ርዕዮት ነው !

1 ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች - Message 3 | Part II 10:36
10:36
التشغيل لاحقا
التشغيل لاحقا
قوائم
إعجاب
احب10:36
ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች - Message 3 | Part II

1 ዛሬ ፥ ጨረቃዋን አይተሻታል ? ...
፩. አዲስ አበባ ፥ ካምፕ አስመራ 3:08
3:08
التشغيل لاحقا
التشغيل لاحقا
قوائم
إعجاب
احب3:08
ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች ፤ Message 3
ራቢራ ሱራ ነኝ ። ቢራዬን እንደትኩስ ሻይ ...
ውብትሽን ከሩቅ ለሚያይ 'ፍዝ' ነው ። ሎሚ እንዳቤዠው ሻይ ፥ ካልቀመሱት የአይን ስህተት ነው ። ይሄን ብዥታ እንደሀቅ ተቀብለው ፥ ይገፉሻል ። ለእኔ ግን ፥ ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ። ከማታውቂው አገር ብትኮምሪ ፥ የቤትሽ የመጨረሻ ሰካራም ፥ እኔ ነው ምሆነው ። ትተሽ ብታዘምሪ ፥ ጭራ ልጌ አጅባለው ። ለእኔ ? ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ። በፀጋ ሆነ ቅባት ፥ ብቻ ከአንዱ ሆነሽ ብትነፍቂ ፥ ጥላ ጥለትሽን ይዤ እከተልሻለው ። አንቺ በምታምኚው ፥ እኔ እታነመናለሁ ። ውርስ ሥጋዬ ለስደትሽ ጌተሴማኒ ነው ። ዘመኔን የታነፅኩት ፥ ከሚያሳዱሽ ምስካይ እንድሆን ነው ። ከሰው አፍ ውለሽ ፥ ከሰው አፍ ብታድሪ ፥ ገመናቸውን በአንቺ አይተው በመላ አገር ብትነውሪ ፥ ኮሶ እንዳገሳቸው ተጨማደው ቢጠየፉሽ ፥ ያን ገላሽን ወደው በያው ገላሽ ቢከሱሽ ... አንችን አስጠግቼ ነውረኛ እሆናለው ። እነርሱ ከገቡበት ገነት ፥ አንቺ የተጣልሽበት ፥ ደይን እመርጣለሁ ። አንቺ ቀርተሽ ፥ ምን ማቅ ኖሮኝ እቀራለሁ ? አግቧቸውን አንገርግሬ ከአንቺው ጋር እጠፋለሁ ። ጣዕምሽን አውልዬ እኔው ነኝ ማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ፤ ከሰው መጥቶ አይደለም ፤ የእውነት ነው ፥ እወድሻለሁ !…
የተንጣለለው አስፋልት በሚረግፈው የዳመና ቡትርፍ እየታጠበ ነው ። አቶ 'ሀ' ( ይቅርታ ፤ ስሙን ስለማላውቀው ነው) ጭር ባለው ጎዳና እየተዘነበበት ወደቤቱ ያቀናል ። ተበታትኖ የሚወርደው የጨፈጨፍ ናዳ ሲያርፍ ይዘልና ሌላ ቀድሞ የወረደ ጨፍ እየያዘ ወደዳር ይንቆረቆራል ። ተርታውን ያቀረቀሩት የመንገድ ዳር መብራቶች ገና ሳይመሽ በስህተት ብርሃናቸውን ወልተዋል ...
ለአዳም ረታ - የልደት ማስታወሻ
የችኮላ ሥራ ሲገጥመኝ ትዝ የምትለኝ ነገር ነች። ቄራ ላይ የሆነ ነው ፥ ያው እንደጨዋታ ። አስኩቲ የሚባል እሳት ሞተረኛ ...
Excerpt : ድምቡሎ ጎዳና | Short story.
ጀግና የወደድሽ ሰሞን ፤ ጀግና አሳድዳለው ። ጎሽ ገድዬ ኮልባ ሎቲ እቀርፃለው ። ከነብር ገላ ላይ ለአንገት በርኖስ እላጫለሁ •••
በመሃል እራት አለመብላቴ ትዝ ብሎኝ ደሞ በባዶ ሆዴ ተከዝኩ ። ችግሮቼ በጣም ስለሚወዱኝ ብቻዬን አይተውኝም ፥ አንዱ እንኳ ሲሄድ አንዱን ተክቶ ነው ....
ይሄኔ ነው ትርዒቱ የተለኮሰው ። መጀመሪያ የበረንዳው አምፖል ላምባ እንደጨረሰ ኩራዝ ጥር ጥር ሲል ቆይቶ ዚግዛጉ እስኪታይ ድረስ ከሰመ ። ተደፍቶ በስንፍናዬ ያልወለወልኩት ውሃን ወለሉ ሲመጠውና ጠቦ ጠቦ ሲጠፋ አየሁ ። በድንጋጤ እግሮቼን ወንበሬ ላይ ሰበሰብኩ ። የግቢያችን መታጠፊያ ሾላ ዛፍ ላይ የተከመሩ ወፎች ተበተኑ ። እነሱን ተከትለው የዛፉ ፍሬዎች ሿ ብለው ረገፉ ....
S
Sost kilo

በሩ ሁለቴ ተንኳኳ ። ስከፍት የበሩን የውጭ ማዕዘን ተደግፋ ቆማለች ። ሰላምታ ሳትሰጠኝ አልፋኝ ገባችና ዘግቼው ወደሷ እስክዞር ጠብቃ " አርግዣለሁ " አለቺኝ ። ደንግጬ አየኌት ....
የለበሰችው እጅጌ ሙሉ ፒትልስ ወልቆ ምኔ እርቃኗን እንደቀረች አታውቅም ። የተጨመታተረው አንሶላው ሀሩር ገላዋን እየነካ ሲቆጠቁጣት ገልፍፋ ጣለችው ....
ከትናንት ወዲያ ማታ ለት እናቴ እሪሪ ብላ እያለቀሰች ገረፈቺኝ ፤ እያነቡ እስክስታ ነገር ። ከደቂቃ በፊት ( ደብተሬ ላይ ጭረት እስካይና እስክጠይቃት) አገር ጎረቤት ሰላም ነው ብለን ስለ ሙሉ ቁጥሮች ተካፋይ ስታስረዳኝ ነበር ። ድንገት ተነስታ ጫማዋን አውልቃ አናት አናቴን እየጠፈጠች < ኧረ ሰዎች አቃተኝ ምናባቴ ላርገው ? > ብላ ለአገላጋዮቼ ታሳጣኛለች ፤ ሁለተኛ በደል ። ባህሪዋ ለማንም ግራ የሚገባ አይነት ነው ። እስኪ ልፈትናት ብዬ ሁለት ቀን የሚያስቅ ቀልድ ባወራት ራሱ ትንሽ ፈገግ ሳትል ወደ ጠብደል ምክር ትለውጠዋለች ። ምክሯ ከመብዛቱ የተነሳ አንዳንዴ እንዲሁ < ዛሬ አመክሪኝም ኣ ? > እላታለው ። በራሷ ስቃ ትንሽ ትቆይና < እናት ላይ እንዲ ማሾፍ ጥሩ ነው ? > ብላ ትጀምራለች . . . ሃሃሃ ..........…
... ረጅም የስደት ሰልፍ ፥ ሰሌን አናቷ ላይ ጠቅልላ የምትጓዝ እናት ፥ የታረዙ ብላቴኖች ፥ የተደፈሩ መበለት ፥ የተገፈፉ ክብሮች ፥ የከተማ ምሽጎች ፥ የተበሳሱ መስኮቶች ፥ የሚነዱ ቲያትር ቤቶች ፥ ከሰማይ የሚዘንቡ አረሮች ፥ በየቀጠናው የተማገዱ ጎረምሶች ፥ ባንጋ የቀላቸው አናቶች ፥ የሰቀቀን እሪታዎች ፥ ጆፌ የሚዞረው አንገት ፥ የልጁን ሬሳ የሚያናግር አባት ፥ ረጅም የእሾህ አጥር ፥ የስጋት ድንኳኖች ፥ ፈንጂ ዶሿቸው የሚደሁ ገላዎች ፥ እሳት አከፋፋይ ኦራሎች ፥ የነፍሴ አውጪኝ ትርምስ ፥ የሚያለቅሱ ቄሶች ፥ ሚናራቸው የወደቀ መስጂዶች ፥ የተጨነቁ ሩሆች ፥ የማይታይ ነጭ ባንዲራ ...…
ሲመሽ – ፊት ላይ የሚለሰልስ ብርትኳናማ የፀሃይ ጨረር ሲፈናጠቅ – ከመስጂድ ሚናር የመግሪብ አዛን ሲሰማ – ህዝቤ ስራ ያንዠረገገው ሚስቶ ፊቱን ይዞ ወደቤቱ ሰከም ሰከም ሲል – የትራፊክና የፍሬቻ መብራቶች መድመቅ ሲጀምሩ – የእራት ወጥ ጢሶች ከየኩሽናው ወደሰማይ ሲወጡ . . . ሲመሽ ፤ ሲመሽ . . . ትዝ ይለኛል . . . !
እንደዛ ነው የሚያደርጉት ፤ ይሄዳሉ ። ምንም ሳይሉህ ይሄዳሉ ። እንደጨረቃ ሙላታቸው ይጎድላል - ይገምሳል - ይቀጥኑ ይቀጥኑና - በሆነ ቀን ቀና ስትል የሉም ። ለመከተያ እንኳ ዳና ሳይተውልህ - ልክ እንደ ወቅቶች ፤ እንዳምናዎች ፤ እንደትናንቶች ... ሄድን ሳይሉ ፥ ፍውው …! በዳ'ባድመ መሐል ጥለውህ ሄደውም እንዳልረሣሀቸው ማወቅ ይፈልጋሉ ። ይሄ መሻት እያደር ሲሞረሙራቸው ረፈዶ ከባቸ በኋላ 'ቻው' ይሉሃል ። ከሄዱ ከምናምን አመታት በኋላ አተኩሰው ይሰናበቱሃል ። ደሞ ቻው ሲሉህ . . . ቻው፡ቻው ! ያንተው ሃና ። …የደብዳቤው 31ኛ መስመር መቋጫ ላይ። ጠርዙን ቴምብር ካሽቆጠቆጠው ቅድ ፖስታ ውስጥ ለመጨረሻ ግዜ አውጥቼ እያነበብኩት ነው ። ስድስቴም ሳነበው በዛው ክልትው ብዬ እንዳልቀር የሞትሞቴን እየተንቀጠቀጥኩ ። የተፃፉት ሆሄያት በህላዌዬ ላይ የተደገኑ ስድር ቀልሃዎች ናቸው ። በየ'አራት ነጥቡ ባለ እረፍት የዳደረ ጠባሳዬ እንደአዲስ ቁስል ይገሸለጣል ። ፊደላቱ ከእያንዳንዷ የመስመር አፎት እየተተኮሱ ደህና የነበርኩትን ሰውዬ በሳሱኝ ። ሽንቁር ልቤን በመዳፌ እንዳፈንኩ ለአንዴና መጨረሻ ግዜ የሠላሳንም መስመር ዝናር አረገፍኩ ። አንብቤ እንደጨረስኩ ርዶ የሚቀጠቀጥ እጄን አየሁት ። በመሃል ጣቴና ቀለበት ጣቴ መሃል በቄንጥ የያዝኩት ሲጃራዬ ቅርጣን ተሸክሟል ። ምኔ ቀድሼ ምኔ እንደማግኲት እንጃ እያለቀ ነው ። ሙት አመዱን አራግፌ መልሼ አጋምኩና አንብቤ የወጣሁትን ደብዳቤ ለኮስኩበት ። የድንገቴ ድፍረቴን ታዝቦ ነው መሰለኝ እንባዬ እንደዥረት ተንፎለፎለ ። መንሰቅሰቅ የለ አፍንጫ መምጠጥ ፤ ስቅታ የለው አይን ማበስ …ያለንጥቀት ፈሰሰ ። […ጭልጥ … በሐሳብ …ጭልጥ በእሣት ውስጥ ] የሚነደው ሉክ የተበሳበትን ቅርፅ ይዞ እየሰፋ ሲቀጣጠል ቁሪ ሲጃራዬን ከእጄ አሸቀነጠርኳት ። ነበልባሉ መሀሉን አጥቁሮ እየቀላ ይነዳል ። ወላፈን ተከትሎት ቀስ ብሎ እየሻረ ወደላይ ተውለበለበ ። ክርር ያለ እሳት እንደሚሆነው አንዴ ሰማያዊ ደሞ ቀይ እየሆነ ። ንዳጁ ሲንቦገቦግ ፊቴና ከባቢው ላይ ብርሃን በብራ ይመላለሳል ። በፊት …ሐኒን ሳቅፋት መሃላችን ከእቶን ይግል ነበር ። ቁጭ ብለን የምፈልገው ሁሉ ይሆናል። አለም እጆቼ ውስጥ ነበረች - ውጪው ብዙም አያጓጓኝም ። እየቆየሁ ግን ከማፍቀር ይልቅ የአጣታለው ስጋት ነብሰስጋዬን ያሟጠኝ ገባ ። አንድ ቀን እንደምንጋባ ሳይሆን በሆነ ለሊት ጥላኝ እንደምትሔድ አስብ ጀመር ። አጠገቤ ሆና የአሁንን ሁነት ከመቅመስ እንዳትሄድብኝ በመፍራት እፍኝ ግዜዬ አለፈ ። ሄደችም ። ጥላኝ በሄደች ባመቱ ችፍችግ ፀጉሬ ሰየበ ። ትካዜ በነብሴ ሁሉም ማዕዘናት ደራ ። በግኑዝ መብሰልሰል የለት ማዕዴ ሆነ ። ወዴትም እንዳልራመድ ትዝታዎች ቅናዋት ሆነው ተቸነካከሩብኝ ። እንደፎቶ አንድ ቦታ ተስቅዬ ቀረሁ ። ከዚያ ወዲህ ያለው ውሏዳሬ አመት በመቁጠር ላይ ተመሰረተ። በአንዱ ቀን ከፀሀይዋ ጋር አብራ የምትወጣ እየመሰለኝ አምሽቼ ተኝቼ ማልጄ እነሳለሁ ። ብዙ ያልታዩ ቲያትሮችን በአይምሮዬ እደርስ ጀመር ። ስልኬ በጠራ ቁጥር ሰርክ እደነግጣለው ። ' እሷ ብቶንስ' የሚል የናፍቆት ስቅቃት ገደለኝ ። ትመጣ ይሆን …አስፋልት ስሻገር አገኛት ይሆን … የምሯን ነው … በማይመለሱ ጥያቄዎች ሙት ልጇን እንዳልቀበረች እናት ሩሄን ስፋቅ ኖርኩ ። […ጭልጥ … በእሣት …ጭልጥ በሐሳብ ውስጥ ] የሉኩን ጩኸት ሰማሁት ጠ'ጠ'ጣ'ጣ ። ጩኸቱን ስሰማ አሳዘነኝ ። በምንተዳው እንደኔ ይቃጠል ።እጄ ላይ እስኪደርስ አቆይቼው ጣቴን ከመለብለቡ በፊት ጣልኩት ።አየር ላይ ሁለቴ ቀዝፎ የወለሉ ሸካክላ (*ceramic) ላይ አረፈ ። እሳቱ እያንዳንዷን መስመር እያጠፋ ወደ ላይ ወጣ ፤ እኔም እሱን ነበር የፈለኩት እያንዷዷን የትዝታ መስመር ማክሰም ። እሳት እንደውሃ አይደለም ሲያሻው ወደላይ ይነዳል ።እንዲ ወደኋላ ሄዶም የነበረን እንዳልነበር ያደርጋል ። ነዶ-ነዶ የፀለመው ለብቻው ተፈረከሰ ። ፍርካሹን በጫማዬ ፊት ሶል አመድ እስኪሆን አሸሁት ። ቃላት ከወረቀቱ በነው እንደጠፉት ከጭንቅላቴ ይደመሰስ ይመስል ። እምባዬ እንዳልቆመ -አሁንም እየወረደ መሆኑን ያወኩት ሸንጎበቴን (* ከንፈር ስር የተሸጎጠ ሪዝ) አርሶ የከሰለው ወረቀት ላይ ጠብ ሲል ሳይ ነው ። ሁሌም ልረሳት ሳኮቦኩብ ከየት መጣች ሳትባል ፊቴ ትደቀናለች ፤ ድምቅ ጥርት ብላ ። ኖራው እንደረገፈ ግድግዳ ቅርጿ ገጦ ይወጣል ። እንዳልረሳኋትና ውኔ ሆን ብሎ እንደሚያደበዝዛት የማውቀው ይሄኔ ነው … ቀለሟኗ ሽታዋ ሳቋን ተከትለው ከች-ከተፍ ሲሉ ። ልቤ እንደሆነ ሲበዛ ደደብ ነው ። ጭንቅላቴ ድሮ ድሮ የተገለጠለትን ዛሬም ድረስ ማመን ቸግሮታል። የገዛ ራስን እንደማሳመን ምን የሚከብድ ነገር አለ በሚካዔል? የዛሬ መጨረሻችንን ብጠላም የምወቅሰው ግን መጀመሪያችንን ነበር ። ምናል ቀደም ባላውቃት እላለሁ ። ከሁለቱ ውጪ በመሀል የነበረን ሁሉ አይፀፅትም ። ህይወቴ እዚች የማትፀፅተው ወፍራም ነጥብ ላይ ነበር ታትማ የቀረችው ። ወላፈኑ የደብዳቤው ቀይና ሰማያዊ ሽልም ላይ በርዶ ጠፋ ። ክሳዪ ጤሰ ።ሲጨስ ጠረኑ ከረገጥኩት ሲጋራ ጋር ተደምሮ በረንዳው ታወደ ። ሽታዋ በሱ ውስጥ ያለ መሰለኝ ። ፅርኒኗ ከልብሶቿ ኮሌታ ላይ አይጠፋም ነበር ። የአንገቷን ላቦት በወረቀቱ እንዳበሰች ሁሉ አሁንም ሽቱዋ አፍንጫዬ ገባ ።… ሳብኩት ። …አሁን የማግኩሽን ልክ ብተነፍስሽ እረሳሻለሁ ። እወድሻለሁ ያልኩሽን ግዜ ልክ ቆጥሬ አልወድሽም ብልሽ ትወጪኛለሽ ። ሁሉንም ብሞክር ይሆናል . . . ? እኔንጃ አይመስለኝም ። [ ለጤናህ እነደምን አለህ ? እኔ ካንተ ሀሳብና ናፍቆት . . . ] አለቺኝ በደማቅ ፅሁፍ ። የእጅ ፅሁፏን አውቀዋለው ጣቶቿን ተጭና ነው የምታቀልመው ። በህይወት ዘመናችን ደብዳቤ ተፃፅፈን አናውቅም ። ደብዳቤ ህግና መስመር አለው ። . . [ውድ ጌታቸው] ብላ ጀመረች ፤ ብላኝ የማታውቀውን ። [እኔ እጅጉን ደህና ነኝ] …ምናምን ። ደብዳቤ አንቀፅ የወቀረው አራት መዐዘን ነው ። ፍቅራችን ህግም ቅርፅም አልነበረውም ፤ ፍሬም አልባ ነበርን ። በአዘቅትም ውስጥ ሆኜ [ውድ ጌታቸው] ማለቷ ፈገግ እንድል ያደርገኛል ። የሀድራዬ (*mood) መለዋወጫ ቁልፍ በእጇ ነው ። ቁልፌን ካስረከብኩ በኋላ የውቃቤዋ ጋን ሆኛለሁ ። እንዳሻት ታደርገኛለች ። ሀተታው እኔን ማፍቀር እንዳልተወች ይናገራል ። እኔ ግን በገሚሶት የምፈቀር አይደለሁም ። ወይ አልነበርኩም ። እንደኔ በቅስበት ሰባቴ ሲናፍቅ ለኖረ ሰው በገሚስ አፈቅርሃለው መባል ቅሌት ነው ። […ጭልጥ …ጭልጥ … በሐሳብ ውስጥ ] እውነት ለመናገር ብዙ አልጠበኳትም ። እንደአጀማመሬ ብጠብቅሽማ ይሄ ደብዳቤም አይደርሰኝ ነበር ። አንደኛሽን በነብስ እንገናኝ ይሆናል እንጂ ። ራሴን ጎዳሁ ። ላክምመውም ብዙ ጣርኩ ፤ አልሆነልኝም ። ትንሽ ሳገግም መዶሻ ይዘሽ ትከተክተቺኛለሽ ። ለቅስም አጥሚት በሌለበት አገር ከተሸረፈ ልብ የተሰበረ አጥንት ማከም ይቀላል ። ትዳር ያዝኩ ።ሌላ የማላውቃትን ሴት ሚስት አድርጌ አገባሁ ። ነዳይ ምን ቢያብድ ስልቻውን አይጥልም እንዲሉ የእናቴን ጭቅጭቅ (ልጄን ምን አዚም አስነኩብኝ ብላ ስታለቅስ ) በሽሽት አገባሁ። ሚስቴ ጥሩ…
ነብሴን በገዙኝ ማግስት የፀሓይን ሞት አረዱኝ ። በከባድ ምጥ ማለፏን እንደሰማሁ በዛለ ጀምበር ወደ ለቅሶው ሄድኩ። መቃብሯ የጀበል ቓፍ (*የምድር ጠርዝ) ኮረብቶች ላይ ነው ።ለቀሥተኛው እየተነዳዳ ወደ ቀብሩ ይግተለተላል። እንደህፃን እግር እየተከተልኩ መጓዝ ጀመርኩ። በገፍ ከሚጋዘዉ ለቀስተኛ እንባ የሚወጣኝ አንድ እኔ ነኝ ። ሌሎቹ የአይን መቅደሳቸው ተገልብጦ ከነጩ መቃድ የጠለሸ ደም ይፈሳል ። ዶቃ ብሌናቸው በቦታው የለም ። ወዮታቸውን ባልሰማም ከደረታቸው የሚነሳ ተደጋጋሚ ስቅታ ግን አለ። እየሄድን ነው ። ከፊቴ የቀደሙም ሆኑ ከጀርባ የተውኳቸው ለቀስተኞች አናታቸው የተመለጠ ሲሆን ከአናታቸው ዙርያ እንፋሎት ይጤሳል ። በተገኘ የገላቸው ቦታ የሞጀጁ ህፃናት ተፈናጠውበታል። የፈላዎቹ አናትም እንዲሁ የተላሰ መላጣ ነው ። ጉዟችን የለቅሶ ነው እንዳልል የምሰማው ዋይታ የለም ። ልንሀጅጅ እንዳይሆን ሀዲስ አይቀራም ። ልቤ ብቻ በጨዋ ሹክሹክታ … ” ዒብሊስ ሊጎርስህ ነው ፣ አምልጥ…አምልጥ ! ” ይለኛል ። (ש) እሣት ፥ ፀሓይ ምሽትን ልትወልድ ያማጠችበት ራማ (ሰማይ) በደም’ዳምና ጨቅይቶ ሰልሟል ። የእንግዴ ልጇ ጨረቃ ግርዶሽ ከልቷት ከእሳት ፣ ከአየርና ውኃ እንደታባች ነው ። መደበቋ ፀሓይን ላለመገነዝ የክህደት አይነት ነው ፤ ያለርሷ ሁለት ለሊት ትቆይ ይመስል ። ገፊዋ ” ምሽት ” ስትማጥ ቆይታ ልክ እናቷን እንደገደለች መዳህ ጀመረች ። የሌቱ ንጉሥ በዙፋኑ ተሰይሞ ማህፀን ቀዳ የወጣችውን ዲቃላ እያየ ነው ። እኔ በርሷ እርጥብ ሽል ውስጥ ነኝ ። (מ) ማይ ፥ በጫካው ስንተም ባዶእግራችን ከሚኮረሻሽመው ርጋፊ ቅጠል በቀር የሚያሰማ ድምፅ የለም ። አልፎ አልፎ ብቻ የሻሿ ንፋስ ይፎጫል ። ተጓዦቹ የገረጣ ፊት ተሸክመው ሲራመዱ ላየ ቅጥባቸው ሳይሞላ አስክሬን የሆኑ ይመስላል … ሰከም ደርግፍ … ሰከም ደርግፍ… ደግሞ ሰከም … ዳገቱን ስቧጥ እንዲደግፈኝ መቋሚያ ይዣለሁ ። በዛም ያለድካም እያቀናሁ ነው ። እንዲ በደመንሚን ስንንጋ’ጋ ከተገተረ ዛፍና ጅብራ የሚጋጭ አልነበረም ። ሁለቱ አይኖቼ የሥውሩን ያህል እርባን የላቸው ይሆን ? በተጓዦቹ ፊት ላይ ላብ ከደም ጋር ተለቁጦ ይንፎለፎላል ። ወደፊት እንጂ እርስ በርስ መተያየት የለም ። ከአሸን ህዝብ መሀል ምንም ያልሆንኩት እንዳሻኝ መዞር የምችለውም እኔ ብቻ ነኝ ። ከነሱ የነሲብ ህመም የኔ ደህና መሆን አስፈርቶኛል … ፈ …ራ …ሁ … ! መሀል መሀላችን የሚልከሰከሱት ውሾች ያነጥሳሉ ። ነብሷን ይማርና አክስቴ የከልብ ንጥሻ ሟርት ነው ትል ነበር ። እሱን ይዤ ጉዞው የመልካም አይሆን ? አልኩ … ወየት እየተነዳህ ነው? ውስጤ ተደርቦ ይጠይቀኛል … ውስጤ እንዲ ነው ክረምቱ ወጥቶ ሲያበቃ አትዘራም ነበር ? የሚል አይነት … አብረን ሄደን ከረፈደ ራሱን የሚያፀዳ …ጣዲቅ ። ንጥቀት ይገትረኝና ስቆም በተቃራኒዬ ከሚጎርፈው ህዝብ እላተማለሁ ። እየፈዘዙ መገተር ካቲዬን በተራማጅ አውራ ጣት ማስቀጥቀጥ ሆነ ። እስከቃንዛዬ ለመቆም ሞክሬ አልቻልኩም ። በዚ ጉዞ መመለስም መቆምም አይቻልም ፣ የሩቅ አሥማት ድግም ነውና ተያይዞ ብቻ እንደመልካ መፍሰስ … አንድ ነገር ገብቶኛል ። በዘፍጥረትና በምፅዓት … በመወለድና ሞት … በመጀመሪያና መጨረሻ … ባለ ሲባጎ ላይ ቆሚያለው ። ሚዛን ጠብቆ መጓዝ እንጂ ይሄም ያልፋል ብሎ ነገር የለም ። እዚህ የግዜ ጠለል ብሎ ነገር የለም … ሰዓትና ቁጥር ውሸት ነው ። ጉብታውን እየተገፋፋን ወጥተን ወደኮረብታው ጫፍ ደረስን ። ጣቶቼ መሀል የላበኝ ላቦት በርዶ ቁር እየጠራ ነው ። ፈርቻለሁ … በጌታ ስም … በጣም ፈርቻለሁ ። (א)አልፋ ፥ እንደደረሰን አንዳንዶቹ ረገዳ (*የለቅሶ ጭፈራ) ጀመሩ ። ሁለት እርምጃ ሄደው እንጠጥ እያሉ እንደመርገፍ ፤ ምን ይሉት ትዕይንት እንደሆን እንጃ ። ለጥቀው የተሸከሟቸውን ብላቴናት የተቦረቦረ ጉድጓድ ውስጥ ይዶሏቸው ገቡ ። ልጆቻቸውን እየገበሩ መሆኑ ነው ። ከገደሉ ጀርባ ባለ ሸለቆ አካይስት ሲንጫጩ ይሰማል ። ወርአበባ ያላዩ አጎጠጎጤዎች ዘነዘና ይዘው የተጣሉትን ማቲዎች ያልማሉ። ሲወቅጧቸው እየዘመሩ ነው .. ኻዩዬ .. የፀደይ ሲሣዬ ላንተ ለሌቱ ጌታ ቃንዛ እስክሥ በኹሉ ፈንታ (እሽም… ምህረት የለም…) ዝንተ’ዛዜል ዝንተ ኅቡኣት አጋናኤል ኽስባዔል ስውራት ። (እሽም… ምህረት የለም…) ኦ…! ዔል ናጴር ቆርጴል ። (እሽም… ምህረት የለም…) ረሐቅ… ሳዶር ረጅ.. አላዶር (እሽም… ምህረት የለም…) ድንጋጤ ዋጠኝ ፤ እይዝ እጨብጠው አጣሁ። ለንሰሃ ብጮህ የምታይ አይመስለኝም … ጥቁር ጉም ወርዷል … እንዳልመለስ ከእውነት አገር በሺ እርፍ ርቂያለው ። ከተራራው ጉልላት ላይ አንዲት ሴት ትታያለች ። ለሌቱ ንጉሥ ሚስቱ አትመስለኝም ፤ እንደ ንግስት ሲያረጋት አላየሁም ። በማርያም ጣቷ ላይ ሴንኬቶ ተቀልብታለች ። ፊቷን ጭምብል ከድኖት አይታይም ። በሚወቀቱት ልጆች ምት ፀጉራን እያሾረች ሹቢሣ ትደነክራለች ። (ሹቢሣ አንገት የማሽከርከር ጭፈራ ነው ።) ደይን (ሲዖል) መድረሳችንን እንዳወቅሁ በሰነፍ አወራወር ጉልበት አጥፌ ተንበረከኩ ። እምነቴ በመንጠፉ መሸነፌን እንደ ማመን … ግዞቱን አሜን ብሎ እንደመቀበል ። እንደተንበረከኩ ከኃኖስ ቃላይ ጠበል ዘነበ ። ጠበሉ ሲዘንብ ፣ ሴቲቱ ጭምብሏን ስታወልቅና ፀሓይ ስትወጣ አንድ ሆነ። ምሽት እንዳሰብኩት ብዙ ይዛኝ አልሄደችም ። ገና እግሯ ሳይጠና ፀሓይ ደምቃ ወጥታለች ። አታለውኛል … ፀሐይ አልሞተችም ። አጃቢዎቼ አይናቸው ሲመለስ የኔ በተራው ለመገልበጥ መርገብገብ ጀመረ ። መራመድ ጀምሪያለው ፣ እየታየኝ አይደለም …አይኔ ተገልብጧል ። የተፈረደባቸው ሲድኑ እኔ ሳልሠረይ ቀረሁ ። በመጨረሻ ቃል ነበር … የተሸጠ ነበስ አይመለስም ። ( ክፍል አንድ)…
የተለያየነው የተገናኘን 'ለት ነው ። እንዲህ እልህ ፍቅራችንን ሳይወርስ በፊት አንዳችን የአንዳችን ደቅ ነበርን ። አሁን በነብስም በስጋም ተለያይተናል ። ሰው ስለይ ጎበዝ እንደሆንኩ እነግራት ነበር ። የትናንት እንጥፍጣፊ ውስጤ አላስቀርም ። ክፉንም ደግ ጠጠር እንደሞላው አቁፋዳ እንዲረሳ አድርጌ ከባህር እሰደዋለው ። አሁንም የሆነው እንደዛ ነው ። ታሪካችን እንደተቋጠረ ቁልቁል ሰምጧል ። ትናንት ሲመሽ እንደሁሌው ጣቶቼን ይዛ አልፀለየችም ። ይልቁን አይኖቼ እስኪከደኑ ጠብቃ የቢጃማዋን መቀነት እየጎተተች ከቤት ወጣች ። አረማመዷ ከመሮጥ ለትንሽ ያዘገመ ነው ። ሻሿ ተፈቶ ከመሬት ሲወድቅ ፤ ፀጉሯ እርቃን ሲወጣ እስከማይሰማት ድረስ ። ዲናዎቹ ሌቱን ሄደችላቸው እንጂ አንዳቸውም ሊይዟት አልመጡም ። ሙራጅ የሽፍታ ሻሞላ ያላደነውን አያርድምናና እነርሱም አራከሷት ። ቢያንስ ቀርድደው እንዲሰቅሏት ብትለምናቸውም ከመሀከላቸው አንድ ሃባ እዛኝ ሳታገኝ ቀረች ። በእንባ የታጠበ ልመናዋ መኖር እንዳገሸገሻት ያሳብቃል ። ሞት ግን የመጣችበትን መንገድ ያህል ራቃት ። አማራጭ እንዳጣች ሲገባት ገለባ ነፍሷን እንደተሸከመች ወደቤት ተመለሰች ። ከጀርባዋ ሲያጅቧት የነበሩ ቁራዎች የጣሪያው ቆርቆሮ ላይ ሲያርፉ ጥፍራቸው ይንሰጠሰጣል ። እንዳልሰማት ዱካዋን በወለሉ እያሟሸች በለሁሳስ አንሶላውን ገልባ ገባች ። እግሯ ይቀዘቅዛል ። ገላዋ ውስጥ የገባው ቁር ከሰውነቷ አልፎ ወደ አልጋው ተጋባ ። ልክ ሽፋሽፍቷ ሲገጥም በተራዬ ተነሳሁ ። የመስኮቱ የግራ መዝጊያ ተበርግዶ ንፋስ ያንሰጠስጠዋል ። የመጋረጃው ዘርፍ ሲውለበለብ የዘለበቱ ጠፍር ከማዕዘኑ ጋር እየተላተመ ይንቋቋል ። ዘላ እንደገባች መልሳ እንዳልዘጋችው ገባኝ ። በድንግዝግዙ ፈዝዤ ደቂቃው ነጎደ ፤ ፅልመቱ ሄዶ አልጎኸም። " ሰዓትህ ደርሷል " ። በውስጤ ያወራሁት ድምፅ አፌን ትቶ በጆሮዬ ወጣ ። ሹክሹክታዬን እንደሰማሁ ከቆምኩበት ወደ ቡፌው ተራምጄ የመሳቢያውን ሰረገላ እንደደገፍኩ ካራ አሰስኩ ። ወዲያውን ፈፀምኳት ። እጄና ክርኔ ላይ የተናጠበው ትኩስ ደም ሳይደርቅ ጨረቃ መግቢያዋን መማሰን ጀምረች ። ፀሐይ ግን ለመውጣት 'ራሱ የወሰነች አትመስልም ። የሰማዩ ውዥንብር የምድሩ ቲያትር ነፀብራቅ ነው ። እጅከፍንጅ የያዘችኝ ቅፅበት በምናልባት ረግታ ለመፍረድ ስታሰላስል ይመስላል ። ሐሙስ ማታ - መዐድ ቀርባ ስትጠብቀኝ የመጨረሻችን ( የመጨረሻዋ ) እራት እንደሆነ ታውቅ ነበር ። ስትስቅ ግን ለዛዋ እንዳለ ነው ። እንደሁሌም ፈገግታዋን ለማገዝ የአይኖቿ ዳር ይሸበሸባል። በአፍንጫዎቿ ጫፍ የአንገቴን ስር ትታከከኛለች ። ምኗም የተረበሸ አትመስልም ። ነገን እንደማትኖር እያወቀች ስለሚፈሰው ደሟ ፅዋ አልቀዳችልኝም ። አታላኛለች ። ረጅሙ ሌት ሟጦ እንደምንም አርብ እስከወጋገኑ ጠባ ። ታጥቦ ያልተወለወለ የሣህን ላብ በመሃረቤ አደራርቄ ጠረጴዛው ላይ አኖርኩ ። የመጀመሪዬን ቁርስ ለብቻዬ እያበሰልኩ ነው ። ህልም የሆነ አዳሬ ረዝሞ እንደማይነጋ ፤ ጭንቀት ሰቅዞ እንዳልያዘኝ አሁን እየተነፈስኩ ነው ። መጥበሻውን አንጋልዬ ዘይት ስጨምር በእሳት የጋለ ልቧ መንቶሻቶሽ ጀመረ ። ይቺ ሴትዘመን ፆሜን ልታስገድፈኝ ነው ።…
የዛሬ ሃያ ዓመት ገደማ ፤ በሆነ በማይታወሰኝ ቀን ከእንቅልፌ ተነስቼ ስንገላጀጅ የግንፍል ሾርባ ሽታ አፍንጫዬን ሰርስሮ ገባ ። ቅንድቦቼን በፍትጊያ አላቅቄ አነፈነፍኩ ' የፈጣሪ ያለህ ፓስቲኒ ነው ። ' ከስጋ ቀጥሎ የምር የምጠላውና - የሚጠላኝ መብል ፓስቲኒ ነው ። የዶሮ መረቅ ቢገባበትማ ራሴን ሲጥ አርጌ የማጠፋ ይመስለኛል ። ሰባት ዓመቴን ልደፍን የቀሩኝ ቀናት ቢሆንም ዛሬም እናቴ ያለሱ ቁርስ ያለ አይመስላትም ። አሰራሩ ቀላል ሆኖ ይሁን ቶሎ ስለሚደርስ እንጃ የቤታችን የጠዋት ጠዋት ሜኑ ሁለት ነው ። የተሰራልህን ፓስቲኒ ወደህ ፤ ወይ ደሞ የተሰራልህን በግድህ ትበላለህ ። ከአልጋዬ ወርጄ በባዶ እግሬ ወዳለችበት ስሄድ እናቴ ደመኛዬን ከመቀቀያው ወደ ሣህኑ ስትገለብጠው ደረስኩ ። የኪሮስን ' ሠላም ሠላም ሓዋ ' ከፍ አርጋ ከቴፑ እኩል ትዘፍናለች ። ወላ እስከጊታሩ . . . ድሪሪን ዲዲሪን ተቐልቀሊ . . . ዲሪሪ . . . ፈውሲ ክረኽብ . . . ድሪን ድሪን ። ደቃቅ ካሮት እና ብትን አረንጓዴ ቅመም ቤዡ ሾርባ ላይ ፈጠው ይታያሉ ። " ዛሬም ፓስቲኒ ነው አደል ? እኔ አልበላልሽም ! ከማክሰኞ ጀምረሽ እያለቀስኩ አስጋትሺኝ ። ትንሽ እንኳ ግን አታስቢልኝም ? " ብሶቴንን ባልሰማ ገፍታ ' ቦንጆርኖ ! ተነሳሽ ጌታው ? ' አለች ሆጵ አርጋ አንገቴን እየሳመች ። ' ማዐረይ እቺን ጭርስ አርገህ ብላ እንጂ የማረግልህን አታውቅም ? ' የዘወትር ማባበያዋን እንደ አዲስ አነበነበችልኝ ። እኔ ብትሰማኝና ብታደርግ ደስ የሚለኝ ይሄን ሾርባ በጭራሽ መስራት ብታቆም ነው ። " ደሞ አዲስ የቬሮና ፓስቲና ነው ቀድጄ ያረኩልህ - መሀሉ ላይ ክብ ያለው ኮኮብ - የኮኮቦች ምግብ ነው - እንዴት እንደሚጥም አንተ ራስህ ነው ምትነግረኝ ። ሂድ ጫማህን አርገህ ና - ረፍዷልኮ ፤ ዳይ ! " ከፓስቲኒው በላይ የሚረብሸኝ የእናቴ የጠዋት ጠዋት ፍጥነት ነው ። ገና በወጉ ሳልነቃ ቡናዋን እስከሶስት ትልስና ቁርሳችንን አብስላ ፤ ትቀሰቅሰኛለች ። በቅጡ ባልነቃ አይኔ አያታለሁ ፤ ቤቱ ውስጥ እንደተርብ ጥዝዝ'ዝ ትላለች ። እኔ ገና አንድ ነገር ሳልናገር ወለል ወልውላ ጥ...ዝ ፤ ሻይ ጥዳ ጥ...ዝ ፤ ሸሚዟን ተኩሳ ጥ...ዝ ፤ ቦርሳዋን ዘርግፋ መልሳ ትከታለች ። ጥዝታዋን ስትጨርስ እንደሮቦት እያሽከረከረቺኝ ዩኒፎርም ታስለብሰኛለች ። እጅህን ከፍ አርገው ፤ እስኪ ዙር ፤ እስኪ ደሞ እየኝ . . . ቤሎ - ቤሎ ! ልዕሎም ናተይ - በል ና እንሂድ ። የኪራይ ቤታችን ውስጥ ያለነው እኔ ማማና ድመታችን 'ፍቅሪ' ብቻ ነን ። ፍቅሪ ፋንዲሻ እየበላች ፓስቲኒን ግን አሽታ ነው የምተወው - እንደኔው ። የቤታችን ብሶት ዋነኛ ምንጭ የማማ ሥራና ውሎ ከጣልያኖች ጋር መሆን ነው ። በፊት ምግባቸውን ስላንገፈገፈኝ እነርሱንም ( ፓስቲኒ በሊታዎቹን ) ጠልቼ ነበር ። ይሄ ጥላቻዬ በባለፈው ቅዳሜ ግሪጎሪ በላከልን የራሊ ግብዣ በአንድ ጀምበር ተነሳ ። የመኪና ራሊውን ካየሁ አንስቶ ወሬዬ ሁሉ ከኢምቤርቶና ከሮቤርቶ ባዛኒ ማን ይቀድማል ሆነ ። እናቴም አድቫንቴጁን ወስዳ ቅዳሜ አብዮት አደባባይ መሄድ ከፈለክ እሷን በልተህ ጨርስ እያለች ሳምንቱን ሙሉ አስወጠቀችኝ ። ዛሬ ፓስቲኒውን በቀስም ብስበው ራሱ እሺ ብሎኝ የሚገባልኝ አልመሰለኝም ። ጠረጴዛው ላይ ነጭ ማንኪያና ጎድጓዳውን ባለአበባ ሣህን ስታኖር የዘቢት ፈገግታ ሰጠኋት ። " እንደነገርኩህ ነው የዛሬው ይለያል ፤ ቀልጢፍካ ብላዕ ሽኮር " ብላ የፀጉሯን ማስያዣ እየፈታች ወጣች ። ያለወትሮዋ ነው ። ሁሌም ቁርሴን ትቀርብና እስካጠናቅቅ ድረስ እያየች ቀይ ቀለም የተቀቡ ጥፍሮቿን ጠረጴዛው ላይ ታንቋቋቸዋለች ። ቋቋታው ከማንኪያው ላይ ስወስድ ካለው ስ...ፕታ ጋር ሲደመር የራሱ ዜማ አለው ። የሆነ ስቅጥጥ የሚል ፤ ዋጣት የሚል ፤ የሚያንገሸግሽ አይነት - ቋኴ♪ቋኴ ስ♫ፕ ቋኴ♪ቋኴ ስ♫ፕ ቋኴ♪ቋኴ ስ♫ፕ 🎶 ። ማማ ረጅም ቀሚሷን እያንሿሿች ስትወጣ ከፓስቲኒው ጋር ለብቻችን ቀረን ፤ ተያየን ። አናቴ ጀርባ ካለች ኩርቢት የተንጠለጠለች ባጆዬን እያስፈተልኩ ብዙ አሰብኩ ። በዚህ ጭንቅ መሀል ሆኜ ወንበር ስር የተቀረቀረ ባለ ረጅም ሂል ቡትስ አይኔ ገባ ። አ. . . ሃ ጭንቅላቴን እያሰራሁት ነው ፤ ይሄን ጫማ ስለሚጠባት ይሁን ስለማትወደው ብዙውን ግዜ አታረገውም ። መፍትሄ ሊሆን ይችላል ፤ እንዴት ? ፓስቲኒውን የአግድም ይዤ ጫማው ውስጥ አንቆረቆርኩት ። ስጨርስ የሣህኑን ጠርዝ ላስኩና አፌን ጠራረግኩ ። የቡትሱ ኣፍ ላይ የተንጠባጠበውንም ሾርባ በሹራቤ አፅድቼ ወደናቴ ሮጥኩ ። ' ማማ ትንሽ ጨምሪልኝ ' የከንፈር ሰም እየቀባችው የነበረውን ከንፈሯን ከፍታ አየችኝ ፤ ግማሹ እንደቀለመ ነው ። አስተያየቷ ሲረዝም . . . አውቃለሁ እናቴ ! ግርምትሽ ይገባኛል - ሰው እኮ ሁሌ እንደምታስቢው አይሆንም ። ይለወጣል ፤ ይሻሻላል ልላት ፈለኩ ። አይኗን ሰበረችና ' አየህ ሁሌ እንዲህ ከበላህ ጠንካራ ትሆናለህ ። ' ከመዳፌ ወረድ ብላ እጄን በሁለት ጣቷ ከባ እያሳየች. . . ' ይሄን ትሞላዋለህ ። የክፍላቹን ትልቋ ልጅ ማናት ስሟ'ማ . . . አዎ : ሳሮን'ን ወላ ትበልጣታለህ ' አለች ። እናቴ በምግብ እንዲህ ትደሰታለች ብዬ አስቤ አላውቅም ። እንደሳሮን ግን መሆን አልፈልግም ። ሙሉ የአጋዚያን ተማሪ ፉስቶ ነው የሚላት ፤ ፉስቶ መባል ማን ይፈልጋል ። ጨራርሰን - ቦርሳዬን አስነግታኝ ልክ ልንወጣ ስንል የት ነበር ያልተባለ ካፍያ በሰያፍ መጣል ጀመረ ። ማማ ' ቆይ - እንዳትወጣ ዣንጥላ ልያዝ ' ብላ ወደውስጥ ተመልሳ ገባች ። በአለላ ቀለም ያሽቆጠቆጠ ዣንጥላዋን ከወሸቀችበት ስታወጣ ከቡትሷ ፊትለፊት ጋር ተያዩ ። አይኖቼ ሰፉ ፤ ጣቴ ቆልፌ ቦርሳዬን እንዳዘልኩ ራድኩ ። ቡኒ ቡትሷን አይታ ያደረገችውን ጥልፍልፍ ሰንደል ገርመም ስታረገው የስንብድ በጮክታ ተናገርኩ ' ኧረ ተይ ረፈደብን ' ። ' አየሩ ጥሩ አይደለም አንተም ኮፍያ ያለው ጃኬትህ አርግ ' ብላ ጫማዋን በቁሟ ፈታ የቀኝ እግሯን ቡትስ ለማጥለቅ ትታገል ጀመር ። ሰቀቀን ገላዬን አኮማተረው ። የቀኟን እግሯን በዚፗ ወደላይ ሾጥ አርጋ አጠበቀች ። ግራዋን እንደማንሳት ስትል ጀርባዬን ሳላዞር ወደበሩ አፈገፈግኹ ። ጭምር ስታረገውና እግሯን ሲረጥባት አንድ ሆነ ። እንደመብረር ባለ አቋቋም ሆና አይኖቿ ፈጠጡ ። በሩ ከፍቼ እየሮጥኩ ወጣሁ ። ካፊያው እየወረደብኝ ቀጭን ጩኸትና ስድብ ሲከታተሉ ሰማሁ . . . ዋ...... ይ ! ማማሚያ - ኼ ካቮሎ! [ Leoulzewelde.wordpress.com ]…
ፅድ አናት ላይ - ሽልም የኮኮብ ዕድ ሳይ - በዝንፍንፍ ቅርንጫፍ የተጥመለመለ ሲባጎ ብልጭ - ድርግም ሲል - የአበርክቶ ሙዳይ ዙሪያው ሲከመር - ዜማ ሲናኝ ፥ በዓመቱ ኦሜጋ ሁሉም ወደልጅነቱ ሲሰበሰብ - በቀለም ያሸበረቁ ህፃናት ተሰብስበው ሲዘምሩ - ኩርሽም ከረሜላዎች አፋቸው ላይ እየሟሟ ሲወልል - ሞሳነት ፍፅምና መሆኑን አምነው ፥ አዛውንቶች በልጆች ሲመረቁ ፥ የበረዶ ጥጥ ብናኞችን አሳበው መላዕክት ሰብ'ን ሲስሙ - የከተማው ካቴድራሎች ስንጉሱ ብስራት ሲደውሉ - የተነጠፉ መንገዶች ሁሉ - ወደቤት አቅጣጫ ሲወስዱ - በብልቃጥ የነበረ መንፈስ ሲተን - ተኖ ቤት ሲሞላ ፥ ብርቅርቅ ኳሶች እየተብረቀረቁ ሲወዛወዙ - ቀያይ ሻማ ዎች ተለኩሰው ሲታወድ - በቁር ቆፈን ውስጥ የነበሩ ጉንጮች መልሰው ሲፈግጉ - ቤተሰብ የታከበላቸው እናቶች አይን - እንደታጠበ ብርጭቆ ሲብለጨልጭ - ሳቆች ተርፈው ወለል ላይ ሲወዳድቁ ፥ በክፍት ልቦች ውስጥ የገባ ንዝረት መልሶ ሲፈስ - ፍልቅልቅ ብላቴኖች ጌታ እንዳየ ውሻ ከግድግዳ ግድግዳ ሲዘሉ ። ነገ ጠዋት - ጦማራቸውን አንብቦ የሚመጣውን ሽማግሌ በተስፋ ሲጠብቁ ፥ ቃጭል ያነገቱ አጋዘኖችን በየብስ ሠረገላ ሲጋልቡ - በራማ ጋሪ ሲከንፉ - ጆንያ ተሸካሚው ሽማግሌ ነጭ ሪዙን እየፈተለ ሲደውል - ቦቲውን እያማታ - በየአጥቢያው ሆ'ሆይ ሲል ፥ ከአንቺ መሆን እመኛለሁ ። አድማስ ተሻግሮ የተኛ ልቤ ቀኑ ሲደርስ ይቀሰቀሳል ። አይኔን ውኃ ይሞላል ። ደሞ ፥ ደሞ መጣ ... Prompt : Carla Thomas - It's Christmas. It's been a long long time , Cant' explain why you crossed my mind I guess it's just to wish you a merry Christmas.…
S
Sost kilo

1 አሁን ምን ያደርጋል የሴት ወየው ባይ፣
ወሎ የመጣው ሞት ሸዋ የለም ወይ? 3:10
3:10
التشغيل لاحقا
التشغيل لاحقا
قوائم
إعجاب
احب3:10
Leoul zewelde | Podcaster : Yeab Dems ምክንያት ይሰጡት እንጂ ፥ ሞት አይቀርም ። ተዘጋጅተው አይጠብቁት ነገር ደግLምክንያትዳ እንጂ ሙሽራ አይደለም ። በጦርነት ግፎች እንደሚሞት ሁሉ በሰላም ውስጥ ተኹኖም ይሞታል ። በረሃብ አረንቋ እንደሚሞት ፥ በጥጋብና አለቅጥ ውፍረትም ይሞታል ። ኤሊያሶች አይደለን አንዳናርግ ፥ ሮሙለስ አይደለን አንሠወርም ። ለማን እንደራራው - ለማን እንደሳሳው ይተወናል ? በአንድ ወቅት የሸዋረጋ ምኒሊክ ፥ የንጉሥ ሚካኤል ባለቤት ፥ ከወሎ አገር መከተሟን ሸዋዎች አልወደዱም ነበር ። ይህ አለመውደዳቸው ከወሎና ሸዋ ባላንጣነት ፥ ማለትም ከልጅ እያሱ መፈንቀለ መንግስት ጋር ይገናኛል ። ታዲያ እመቤቲቱ በጠና ይታመሙና ይሞታሉ ። ያን ግዜ ታዲያ ሸዋ ሙሾ አውራጅ ከወረኢሉ ይሰዳል ። ሴቲቱም ... በቀረብሽ ምነው ፥ ከወሎ ጋብቻ ፥ በወሎ ግዛት ፤ ወጣ እንዳለች ቀረች የሸዋ እመቤት ። እያለች ህዝቡን ታስለቅስ ገባች። ለዚህ መልስ ፥ በለቅሶው ላይ የነበረ ወለየ ፥ የመግቢያዬን ርዕስ ተቀኘ - አሁን ምን ያደርጋል የሴት ወየው ባይ፣ ወሎ የመጣው ሞት ሸዋ የለም ወይ? ተይ አንቺ ሴትዮ ነገር አታጥብቂ ፣ እኛ አልገደልናትም እግዜርን ጠይቂ ። ሰው ፥ ከሞት በኋላ ባለው ሕይወት አመነ አላመነ ከመሞት አይቀርም ። ከመካከለኛው ምስራቅ የፈለቁ ሀይማኖቶች የሞት ምክንያት ከዕፀ በለስ ጋር ሲያቆራኙ ያ ወለየ ግን እስኪ ምናልባት እስኪ እግዜርን ጠይቁ ብሏል ። እንጠይቅ ? ብቻ ጠየቅን አልጠየቅን ፥ ሞት ይመጣል ሃሃ ። ማድረግ የምንችለው ፥ ቢያንስ መልዓከ ሞትን ማዝናናት ነው ። በAppointment in samarra - ኢራቃዊው የነጋዴ ተላላኪ ኒቃብ ያደረገች መልዓከ ሞት በባግዳድ አይቶ ወደ ሣማራ ሄዶ ይደበቃታል ። ይሄ ያየች መልዓከ ሞት ታዲያ በዚህ ተዝናናች ፥ ደስም አላት ። በመዝናናት ውስጥ ሆና እንዲህ የተቀኘች ይመስለኛል ፥ ከነጋዴው ፈረስ ፥ የተበደርከው ሣማራ የለም ወይ ፥ ከባግዳድ ያለው ?…
S
Sost kilo

1 የ አ ረ መ ኔ ፡ ክ ር ስ ት ያ ኖ ች ፡ ዘ ር ፡ ማ ጥ ፋ ት 5:29
5:29
التشغيل لاحقا
التشغيل لاحقا
قوائم
إعجاب
احب5:29
በመካከለኛው ዘመን ፥ አውሮጳ ግሪጎሪ ፱ኛ የተባለ ድመት ጠል ጳጳስ ትቀባለች ። ይህ እብሪተኛ ሰው በትረ ሙሴውን በጨበጠ ማግስት በፀሊም ድመቶች ላይ የዘር ማጥፋት (*Pogrom) አወጀ ። ይሄ አሰቃቂ የእልቂት አዋጅ በድመታውያን ታሪክ በክርስትያኖች የተፈፀመባቸው ትልቁ በደል ነው ። ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው ። ተራማጅ እንደሆነ በአንደበቱ የሚናገረው ጳጳስ የጵጵስና ማዕረጉን ያገኘው በልጅ እግሩ በሰማንያ ዕድሜው ነበር ። መንበሩን እንደተቀበለም እረፍት አጥቶ ቀኖናዎችን ያሻሽል ገባ ። መታተሩንና እረፍት ማጣቱን ያዩ ሮማውያን የለውጥ ሐዋርያቸው አድርገው ተቀበሉት ። ለፍቅርና እምነት የተቀባው ጳጳስ ግን ነገረ ሥራው በየዓውደምህረቱ ፀሊም ድመቶችን መገዘትና ወግዝ ማለት ሆነ ። በ(* Vox in Rama' ) አጀንዳ የዚች ሀገር ሀጥያት ተሸካሚዎች እነርሱ ናቸው ሲል አስተላለፈ ። እነዚህ እርኩሳን ከቅድስቲቷ ሀገራችን ካልወጡ ቡራኼ አይሰፍንም ። ያለፈው የጨለማው ዘመን መለወጥ አለበት ብሎ ለፈፈ። መሳፍንትም ከአፉ እየተቀበሉ ዲስኩሩን በየአጥቢያው ይጎስሙ ገቡ ። ፈሪሃ እግዛብሔር አድሮበታል የሚባለው ህዝብም ፀሊም ድመቶች እያደነ በየአደባባዩ ዘቅዝቆ ይገድል ጀመር ። አማኞች ድመቶችን በቤተልሔም አፀድ ውስጥ በደቦ ወግረው ገደሏቸው ። ጎረቤቶቻቸው በቁም ሲነዱ ያዩ እያዩ የነበር አዳዲ (ነጫጭ) ድመቶችም አልቀረላቸውም ፤ የነርሱ ቤትም ተንኳኳ። እያደር ወደመላው የድመት ዘር ጭፍጨፋ ከፍ ብሎ ተዘመተ ። ለአይን የሚያሳሱ ከምስር (ግብጥ) የመጡ ባለፈር ድመቶች በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደአለባ ጤዛ ረገፉ ። የስንቱን እህል ጎተራ ደህንነት ከአይጥና መጎጦች ሲጠብቁ የነበሩም የደህንነት ስጋት ናችሁ ተብለው ታረዱ ። በአፍቅሮተድመት የነሆለሉ መናኩሳትና ጋለሞታዎች ከደበቃቹበት ውለዱ እየተባለ ቤት ንብረታቸው በእሳት ተለኮሰ ። ወቅቱ ፲፬ ክፍለዘመን እንደመሆኑ የስልጣኔ ጥንስስ እርሾ የሚነሰነስበት ፤ በየ ተማሪ ቤት የሐሳብ ክርክር በአመክንዮ የሚደርግበት ቢሆንም ጥላቻ ምንንም የመጋረድ ሀይል አለውና ፤ አውሯቸው ነበር ። በጥቂት ግዚያት ውስጥ " የዲያቢሎስ ገረድ " የተባሉት ፀሊም ድመቶች ደብዛቸው በአውሮጳ ከሰመ ። የአንዱ ለሊት ላንዱ ፀሐይ ነውና አይጦች በተራቸው ብራ ቀን ወጣላቸው ። የዋህ ጥቁር ድመቶች ሲያልቁ ከይሲ ጥቋቁር አይጦች በአእላፍ ረቡ ። ዘና ቀብረር ብለው በአደባባዩ ይንጎማለሉም ጀመር ። ጠዋት የቀመሱትን ማታ የማይደግሙ ቅንጡዎች ሆኑ ። ድሎት ገንፍሎ አሰቃየቸው ። እጅግ በሚዘገንን ሁኔታም ተራቡና አውሮጳን ከግር እስከራሷ ወረሷት ። ማኛ ማኛውን እህል እየመረጡ ፈጁ ። ረግረግ የጀልባ ጣውላ እየቦረቦሩ ብዙውን የባህር ነጋዴ አሰመጡ ። ቀስ እያሉ ደሞ ወህኒ ቤት የታጎሩ ፍርደኛ ሰዎችን መቦደስ ጀመሩ ባስ ሲልም ይበሏቸው ነበር ። የከፋው መዘዝ ግን ይሄ አልነበረም ። የጥቁር ድመቶች አምላክ ጥቁሩን መቅሰፍት " Black Plague " ላከባቸው ።የጥቁር ድመቶች እልቂት ሌላ ጥቁር ሞትን ወለደ ። በዚያ ምድር ታይቶ የማይታወቅ አስከፊ የሰደድ በሽታ መጣ ። ሰደድ በሽታውን አይጦች እየዞሩ አዛመቱት ። ጥፋቱ የእያንዳንዱን ቤተ ጓዳ አንኳኳ። ባገሩ ድውያን ከጤነኞች በዙ ። ገሚስ አውሮጳ (ወደ ሁለት መቶ ሚልየን ሰው) ተፈጀ ። ነደድ ቁጣው ክፍለሀገራቱን ሁሉ አዳርሶ ተ'እስያ ድረስ ገባ ። በዚህ ግዜ ተራማጅ ጳጳሳቱና መሳፍንቱ ደነገጡ ። ሰላምና ጤና የራቀው ህዝብ መልሶ ሊበላቸው ሆነ ። ምዕመኑ ፀሎትና ምህለላ እንዲገባ ተነገረው ። የደጀሰላም ደውሎች በቀን ስድስት ግዜ ይደወሉ ጀመር ። ወደላይ ተለቀሰ ፤ እንደታሰበው ግን ለውጥ አልመጣም ። የተፈጥሮ ቁጣ ከሰውሠራሽ ይከፋል ፤ እንደው ታሳባለህ እንጂ የምትከሰው አይኖርህም ። ነገሩ እየበረታባቸው ሲሄድ መሳፍንቱ ሌላ ማምከኒያ (*False flag) ፍለጋ ዶለቱ ። ሌላ አሳዛኝ ጥፋት ደሞ ተከተለ ። አናሳዎች *Scapegoat ሆኑ ። ረዳት አልባ ምስኪኖች ታሰሱና ነገር አለሙ በነርሱ ተላከከ ። በቤታቸው ውስጥ የድመት ሬሳ እያሰገሩ የችግራችን ምንጭ እነርሱ ናቸው ብለው አስወሩ ። የየአውራጃው መሳፍንት ሁሉ እየተነሳ ህዝቤ ሆይ ዙርያገባህን ጠብቅ አለ ። እግዚያብሔር የመጤና ሰፋሪዎችን መኖር አልወደደም ተባለና የስቃይ መስቀሉ ወደ በከሀዲነት የተፈረጁ ይሁዲዎች ፣ ወደ ፀጉረልሙጥ ተብዬዎች እና ጠንቋዮች ዞረ ። እነሱም አለ ሀጥያት ይሳደዱ ገቡ ። ሰው የሚበዛባቸው ትላልቅ የንግድ ከተሞች ፥ የሬሳ ማጎርያ ሆኑ ። ጥቁር ድመቶችን ሆነ የትኛውንም ፍጡር መጥላት ብሎም ለማጥፋት መነሳት ዕዳ መሸመት ነው ። የሚያስከፍለው ዋጋም ብዙ ነው ። ----------------------------------------------------------- Happy Blackcat awareness month 🖤…
የክብ መጨረሻ ፥ መጀመሪያው ነው ።
S
Sost kilo

1 ያን ቀን ባታቆላምጪኝሥ? | ያልተላኩ አምስት መልዕክቶች ፥ መልዕክት - 2 9:13
9:13
التشغيل لاحقا
التشغيل لاحقا
قوائم
إعجاب
احب9:13
ያ ን ፡ ቀ ን ፥ ባ ታ ቆ ላ ም ጪ ኝ ስ ? [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ] ከወፍራም ብርጭቆ ላይ እያበረደች የምትቀምሰው ወተት የከንፈሯን ዳር በስልባቦት ይኩላል ። የአፏን ወተት ለመግፈፍ እጄን ሰድጄ ግልፋፊውን በጣቴ አስቀረሁ ። ያስቀረሁትን ቀመስኩ ። የላስኩትን ኬሚስትሪ ጣዕም ለማስረዳት ይቸግራል ። ሀይድሮጅን ደርድረው በቦንድ ቢስሉት ዘርፉ ከአሮጌ ዋርካ ይገዝፋል። ቤሎንዥ ፥ ዛሬ ንጋት ላይ ከፓሪስ-ቻርል የገባች ነው ። ስለሚደክም ፥ ችላ የምትመጣም አልመሰለኝም ነበር ። ለገሃር ሳባ ኬክ ቤት ተገናኘን ። ሳፊ ወተት ጋበዝኳት ። ግብዣው የይቅርታ ነው ። ከአምስት ቀን መዘጋጋት በኋላ የሀቅ ኩርፊያዬን ካድኩ ። ጥፋቱ የርሷ ሆኖ የይቅሩ ምንጭ የፈለቀው ከእኔ ነው ። ለምን ? ለሚል ጠያቂ ፥ በቃ ተፈጥሮ አንድ ህግ የላት (አጭር ቀጫጫ መልስ ፥ ሃሃ) ። ጉንጬን ነፍቼ ለጠፉት ውድ ቀናት ራሴን ገስፄ ፤ ማሪኝ አልኹ ። ኩርፊያ የአፍቃሪ ወጉ ቢሆንም ለርሱ አልታደልኩም ። ኩራቴን ገርስሼ ...የኔ ቤሎንዥ ፥ ስላጠፋሽ መልሰሽ እኔኑ ማሪኝ ፥ ከወዲህ አትያዢብኝ ...አልኩ ። ማህተም ሳያገኙ ልብን ከሰጡ እንዲ ነው ፤ የቁልቋል ማሳ ውስጥ እንደለቀቁት ፊኛ ። ካሁን አሁን እሾህ ወጋብኝ እያሉ ንፋስን ሲማፀኑ እንደመኖር ። ጧ'ን ላለመስማት ጆሮን ከድኖ በነሲብ እንደመከተል ። ዉል አልባ አፈቃቀር ፥ ተሳደው የሚያሳዱት ፍቅር። ታድያ ግን ያነጫንጫል ። መነጫነጩ ብዙ ሳይበስል እንደዛሬው በውስጥ ተግሳፅ ይሻራል ። ሽረቱ ርትዕ ስላልሆነ ቁስል ይተዋል ። ቁስሉን ደግሞ ...ቁ...ል...ም...ጫ...ያክመዋል ፥ ያው ከጠባሳ ባያድንም ። የኔ ቤሎንዥ በቃላት መጮት ትወዳለች ። የቃሎቿ አያይዛ ትርጉም የምትመሰርተው በፈገግታዋ እርጥበት ነው ። ሁለት ነጥብ ይሉትን ስርዓተ ነጥብ ለእንደኔ አይነቱ ፋራ ይተውታል ። የምትመሰርተው ንግግር ከደራሲ ተረክ ይረቃል። ደብተራ ፍቆ ቢደግምባቸው ከሰማይ አንድርቢ ያወርዳሉ ። መሳፍንት ድምፇን ተውሰው ክተት ቢያውጁ ዲዳ እንጂ ማንም አይወሰልትባቸውም። ከሁሉ ስሜን ስታቀብጥ ደስ እሰኛለሁ ። ቀድሳ ስትጠራው እንዳጣፈጠኝ በታምቡሬ ልሞ ይወርዳል ። ሲወርድ ከሆዴ የታፈነው መውደድ እንደቫይረስ እየተጋመሰ ራሱን በራሱ ያበዛል ። መጀመሪያ አቆላምጣ የጠራቺኝ የዛሬ ዓመት ክረምት ፥ በስልክ ሽቦ ወስጥ ነው ። በቅጡ አልሰማኋትም ፥ ደረቴ ተረብሾ መሸከም አቃተኝ ። ላይፈነዳ ነገር እየተብላላ አንጀቴ ውስጥ የሚፈላ ዩራንየም ሆነ ። ቤት ለእራት ስቀርብ የውስጤ ውሮ ወሸባ ከፊቴ እንዳይነበብኝ ፈራሁ ። እየበላን አባቴ ፊት መዝለል ሁሉ አሰኝቶኝ ነበር ፥ሃሃ ። ከእጄ የነበረው መፍትሄ ሳይክሌን ይዞ ከቤት መውጣት ነው ፤ ወጣሁ ። እንደጣቃ ጠቅልዬ ያፈንኩትን ስሜት አስፋልት ላይ በትኜ ፥ ወዴት እንደሆነ ሳላውቅ ፥ በሰርክ ውርጭ እየተገረፍኩ ፥ መሪዬን ለቅቄ ስሟን እየጠራሁ ... ጋ... ለ... ብ... ኩ ... ። ሄጄ-ሄጄ የማላውቀው መንገድ መሃል ሰስደርስ ድንገት ወደ ራሴ ተመለስኩ ፥ አማትቤ እየዘነበብኝ ወደቤት ስመለስ ትንሽ ቀዘቀዝሁ። የካፌው ጫጫታ (የወራሪ አንበጣ ድምፅ አይነት ጥዝታ) አልረበሸንም ። በኩርፊያዬ የመጣ ኩርፊያዋን ማሳረጊያ ብዙ አወራን ። ደሞ ብዙ ዝም ብለን ተያየን ፤ አይኖቻችን ውሃ አዝለው እስኪያንፀባርቁ። በዝምታ ስታየኝ ከአርያም ወድቃ መሄጃ እንደጠፋባት መሊክ ነው ። መተያየቱ እንዳበቃ ስፈራ የኖርኳቸውን ሚስጥራት ለመንገር ወሰንኩ ። እንደፋርሰ ዕፅ ህቡዔን ምን እንዳጦዘው እንጃ ሌላ ግዜ የሚከብዱኝ ሶስት ቃላት እንደነገሩ ተወረወሩልኝ ። ከቤሎንዥ ጋር የሚለየን ይሄ ነው ። አያሳስበኝም እንጂ (ወይ ማሰብ አልፈልግም) ከርሷ ቃል ላይ ሁሌም ነብስ ይጎድላል ። ቃሎቿ ቢያምሩም ፥ እዛው አፏ ውስጥ ነው የሚጋገሩት ። እዛው ተመርቶ ከሰዓት መርካቶ ሃሃ ብዕሬ ሶስተኛውን ከስኒው ስር በነበረ ቅዳጅ ሶፍት ላይ ደምቶ እንደጨረሰ 'ኦ! መሄድ አለብኝ' አለች ። ሁለቱን በቅጡ ያየቻቸው አልመሰለኝም ሶስተኛው 'Moi-même a besoin de toi' ...ቤሎንዥ ፥ ታስፈልጊኛለሽ የሚል ነበር ። እሱን በደንብ አይታዋለች ። -ትንሽ አትቆዪም ? አልኹ ለአመል -ኖ ፥ ሌላ ቀን ። አሁን ልሂድ ውስጤ እንሂንም ደቂቃዎች ከሱ ቀንሳ የሰዋችልህ እርሷ ሆና ነው ይለኛል ። ሌላ ግብዣ እንደሚጠብቃት አውቃለሁ ፥ የባሏ እራት ። ( ለካ ባል እንዳላት እስካሁን አልተናገርኩም ፥ የኔ ነገር ) በባሏ አልቀናም ። አንድ ነገር ግን ይረገርመኛል ስማችን አንድ ነው ። ታዲያ ቀጥሎ ምን ያሳስበኛል እርሱንም ለኔ በሰጠችው ቁልምጫ ትጠራው ይሆን ? ... (አፍቃሪ አያስበው የለ) የቁልምጫዋ ስግብግብ ነኝ ። ከኔ ውጪ ማንም እንድትጠራበት አልፈልግም ። እናም አስባለው እሱንም እንደዛ ትለው ይሆን ? ... በሆነ ቀን የእጅ ስልኳን እንደያዘች እየተላፋን ነበር ። የስልኳ መተየቢያ ስሜን ሸምድዶ ኖሮ የስሜን የመጀመሪያ ቃል ስትጫን በራሱ ተሞላ ። ይታይ ፥ አሁን ሰው በዚህ ይደሰታል ? ልቤ በጮቤ የወር ቀለቡን ሰፈረ ፥ ጌታን ። Bonsoir ! ብላኝ እንደወጣች ከአይኔ እስክትጠፋ በካፌው ሻተር አሻግሬ ተከተልኳት ። አብራኝ እንድትሆን ብዙ ተመኝቼ ነበር ። ከሷ ሆኜ የምገድላቸው ሰኮንዶች ሰማይ ቤት ታስበው ቢቀነሱብኝ አይቆጭም ። እንዲህ ባሉ ቀናት ፥ ብቻዬን ስትተወኝ ውስጤ የሚቀረውን ስሜት አልወደውም ። የልቤ ዙርያ ይንቦለቦላል ። የት እሄዳለሁ ፍቅርን እንደረኛ ገሳ ለብሼ አልጠለለው ፥ ሮጬ አላመልጠው ነገር ። በአፍታዎች ውስጥ መልሶ ከፋኝ ። ሀድራዬ እንዲህ ነው ፍቅሬን ሳይሆን ማፍቀሬን ያስረግመኛል ። ልቤን የሆነ መካነ ልብ አዘጋጅታ ብትቀብረው አልኹ ። እንደዛ ሆኖ በወጣልኝና ያለእንባ የደስታ ጉንጉን ባስቀመጥኩ ። ካፌው ውስጥ ሳልንቀሳቀስ እንደደረቅሁ ለአራት ክፉ ሰዓታት ተቀመጥኩ ። አስር ደቂቃን ጮቤ ረግጦ ለሁለት መቶ አርባ ደቂቆች በልዕለ-እሳቤ ተወጋጋሁ ። ጉዳቴን መልሳ እንድታክመኝ አልፈለኩም ። ከሁሉ ቃላቶቿ ያስቀይሙኛል...ሜርድ ! ። ልነግራት ስልኬን አወጥቼ የመልዕክት መላኪያውን ከፈትኩ ። - Toujours à jouer avec les mots ቤሎንዥ ፥ ሁሌም በቃል ትጫወቻለሽ ። ማስወንጨፊያውን ከመጫኔ በፊት አሁን እንዴት ትሆን የሚል ሀሳብ ሰረቀኝ ። ከአቶ ባል ጋር እየተሳሳቁ ? እየሳማት ? ተኝተው ። ራሴ ለራሴው ሲያሰጣኝ ደግሞ በፀሊም ድምፆች ይቀጣኛል ። ለባሏ የነፈግከው ክብር ፣ የጣስከው ህግ ፣ የረገጥካት ሞራልን እያጣቀስክ አስብ እንጂ ...ሰልፊሽ ። የመላኬ የመጨረሻዎቹ ቅፅበቶች ላይ 'ስልኳ በርሱ እጀታ ላይ ቢሆንስ' የሚል ሀሳብ ገብቶ ነገሬን ቀያየረው ። ባሏ ቢያውቀኝና በወንጀሌ ባጣትስ ? እሳቤዬ እንደጎመዘዘኝ ዋጥኩ ። ሸምጋይ ጓደኛ እንኳ የለን ። ደሞ ኋላ በማን ላስለምናት ነው ? በእንዲ እንዲ ጣዖቴ እንድትቆጣ አልፈቀድኩም ። እየተጣሉ ማጣት አለመፈለግ ምን እንደሆነ እንጃ ፥ አላውቅም ። የተየብኳቸውን ፊደላት ግን አሟጥጬ ሰረዝኩ ። ቤ ሎ ን ዥ ፥ ታ ስ ፈ ል ገ ኛ ለ ች ።…
ሌላ ያልነገርኩሽ ፥ የልደትሽ ቀን አበባ ገዝቼ ነበር ። አዎ ! እኔ ። የሚገርምሽ ባገሩ እንደጠፋ ሁሉ የትናየት ሄጄ መሰለሽ ? መጨረሻ ላይ ወሰን ምናምን እሚሉት ሰፈር ትንሽዬ ኪዮስክ ውስጥ ትልቅ መቀስ የያዘች ሻጭ አየሁ ፤ ፈንታቸው መርገፍ የሆኑ ቅጠሎችን እየከረከመች። እንዲሁ ልጅ ሳለሁ ፥ ከትምህርት መልስ ሙሽራ የሚሉትን አበባ ከሰው አፀድ ቀጥፌ ወደቤቴ እሮጥልሻለሁ ። ቤት ልደርስ 'ከባቢ እጄ ከአበባው ተሻሽቶ ኖሮ ፥ ወየበ ። ከቆረጡት ኋላ ቶሎ የሚሞት አይነት ዘር ሆኖም ይሆናል ። ብቻ እጄ ላይ ከስሞ ፥ ነደደኝ ። የቀጠፍኩት እንዲያ እንዳማረበት ለ'ናቴ ልሰጣት ነበር ። ያም ሆኖ አልተውኩትም ። ከስራ መምጫዋን ጠብቄ (አስራ ሁለት ሰዓት እንደምንም ሞልቶልኝ) ሰጠኋት ። የኔ ንጉሥ ብላ አቀፈቺኝ ፥ ከመቀበል ያለፈ ቁብ ሳትሰጠው ። ጭራሽ ወርውራው መክሰስ መብላቴን እየጠየቀች ወደቤት ይዛኝ ገባች ። እጄን ይዛኝ ስትዘልቅ ፊቴ ወደወደቀው አባባ እንደዞረ ነበር ። እናልሽ ቤሎንዥ... ኪዮስኩ ውስጥ ያለችው ልጅ የሚቀባውን ነገር ቀብታ የሆነ የሚነፋ ነገር'ም ነፍታበት አጋጊጣ ምናምን ሰጠችኝ ። እንዴት እንዳማረበት ። ገዝቻት ስወጣ አመስግኜ ፥ መልካም በዓል ! አልኹ ። የምን በዓል ደሞ ? በሚል ግርምታ ታየሁ ፥ ሃሃ። እዝነ ገመዴን ከጆሮዬ ስላልተነሳ ዘፈን እንደምሰማ ሁሉ ምንም ሳልል እግሬን አዙሬ መንገዴን ጀመርኩ ። ለካ ሌላ ሰው የአንቺን ልደት አይቀድስም ። የለም? ፥ ለካ የነሱ ካለንደር በንግስሽ ቀን አይዘጋም ። ከናቴ ለጥቆ አበባ ልሰጠው የነበረው ላንቺ ነበር ። የገዛሁት አበባ በትራንስፖርት ግፍፊ እንዳይጎዳ ወክ ማድረግን መረጥኩ ። አበባውን እንደያዝኩ ይዤ በቀትር ስንከላወስ አላፊ መንገደኛ እያየኝ በልቡ የሆነ ነገር ይላል ። መቼም አበሻ "ምኗ እድለኛ ነች ፥ አበባ የሚሰጣት " ማለት አይቀናውም ። ...አ...ዬ ባህላችን.. ገለመሌ ...እያሉ ይሆናል ። ሰባት ሰዓት ላይ የሜክሲኮው ቶታል (ቦንዡ ካፌ) ደረስኩ ። ተረከዜን ከማቃጠል ውጪ በጉዞው ብዙ አልተሰማኝም ። ትዝ ይልሽ ከሆነ አራቴ ስደውልና በአምስተኛው ጥሪውን ስትጠረቅሚው ፥ እዛ ቁጭ ብዬ ነው ። ከተቀመጥኩ ሰዓት ሊደፍን ምናምን ደቂቃ ሲቀረኝ ያ...!...ሜሴጅ ገባ። - Sorry, Je ne peux pas venir. መምጣት አልቻልኩም ። እንደው እንደቀላል ፤ የአንድ ግድንግድ መፅሀፍን ግፍ በአንድ ነጠላ መስመር ። አለ አደል ፥ ሲቻኮሉ ከሰው ተገጫጭተው ይቅርታ እንደመጠየቅ አይነት ያለ ። እና አበባው ሳይደርስሽ ከእጄ ቀረ ። እናቴም ያኔ አበባውን ስሰጣት እንዴት ሆኜ እንዳመጣሁት አልጠየቀችም ። ማለት ፥ ስላልጠየቀች ለመቅጠፍ የከፈለኩትን መስዋዕትነት አልተረዳችም ። በልጅ ሩሄ አበባ ያህል ነገር ከሰው አጥር ላይ አርጄላት ፥ በቅጡ እንኳ አልባረከችኝም ። ከንቱ ድካም ነበር ። አበርክቶቴ መገፋት የጀመረው ከያኔ አንስቶ ነው ፤ እርኩስ እንደሚሠዋው በግ ፥ እሳት ከራማ ወርዶ እንደማይበላው ...። የዛን ቀን እራሮቴ ተፈቅፍቆ ከልቤ አልወድቅ አለኝ ። የልደትሽ ቀን ባለፈ በሆነኛው ቀን ስልኬን አውጥቼ መርዕዩ ላይ Qu'est-ce qui ne va pas entre nous , bel ange? ብዬ ፃፍኩ ። ችግራችን ግን ምን ነበር ...? ችግራችን ፥ የፍዮሪ በእጄ ላይ መሞት ሳይሆን ፥ ተቀባይ ማጣት ነው ። አንዳችኝ ጉም ሰንጠቀን አንዳችንን ከህዋ ስናስስ ሌላችን ጣርማበር ጓሣ ውስጥ ለሽ ብለን ነበር ። በተራሽ ደሞ አንዳችን ባነን ሌላችንን ስናስስ የሂማልያ ክምር ጋርዶን ለአይን እንሰወራለን ። መልሱን እያወቅሁ ያረቀቅሁትን ጥያቄ ላንቺ መላክ ?አልፈለኩም ። ከደመና በታች እንደቀረ ፀሎት ፥ ካፍ እንዳልወጣ ቃል ፥ እንዳልተኖረ ምኞት ፥ ሲባኑ እንደረሱት ህልም ፥ ደርሰው እንዳልሰበኩት ወንጌል ... በድህሪት መደለዣ የፃፍኩትን የቃላት ድርድር አንድ በአንድ ከስልኬ መርዕይ ሰረዝኩ ። ሰሌዳው እስኪራቆት ፤ የመተየቢያዋ ከርሰር ግራዋን ሄዳ ውልብ ውልብ እስክትል። ፥ እ ...ን...ዲ..ሁ •••| ------------------------------------------------------------ ያ ል ተ ላ ኩ ፡ አ ም ስ ት ፡ ቴ ክ ስ ቶ ች [ M e s s a g e -1 ]…
مرحبًا بك في مشغل أف ام!
يقوم برنامج مشغل أف أم بمسح الويب للحصول على بودكاست عالية الجودة لتستمتع بها الآن. إنه أفضل تطبيق بودكاست ويعمل على أجهزة اندرويد والأيفون والويب. قم بالتسجيل لمزامنة الاشتراكات عبر الأجهزة.